Monday, May 4, 2015

ሊቢያ ላይ ከተሰዉት ሰማእታት መሃል አንዱ ለክርስትያን ወገኖቹ ጥብቅና የቆመው ''ጀማል ራህማን'' ይባላል ተብሎ ሲወራ ነበር ..... አሁን አሁን እየወጡ ያሉ መረጃዎች ግን ሌላ እውነት ይዘው መጥተዋል..... የዳንኤል ክብረትን ፅሁፍ እንጋብዛቹ. . . . ጀማል ራህማን ማነው ???


source : Daniel Kibret ....https://www.facebook.com/tsilat23?fref=nf
‹ጀማል› የተባለ ሙስሊም ወንድማችን በሊቢያ ከተሠዉ ክርስቲያኖች ጋር አብሮ ተሠዉቷል እየተባለ ሲነገር ቆይቷል፡፡ በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞችና ሌሎችም የቅርብ ምንጮች ታሪኩ የተሳሳተ መሆኑን ቢናገሩም ሰሚ ለማግኘት ግን አልተቻለም፡፡ አንዳንዶቹም ታሪኩን የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ፍቅር ማሳያ አድርገው ተሟግተዋል፡፡ እንደ እኔ ግን ይህንን ታላቅ ፍቅር ለማሳየት ‹ጀማል› የተባለ መሥዋዕት መፍጠር አያስፈልገንም፡፡
ፍቅሩ ነበረ፤ አለ፡፡ ተጨማሪ ፈጠራው አያስፈልገውም ነበር፡፡
‹ጀማል› ነው ተብሎ ሲነገርለት የነበረው ወንድማችን ግን ኤፍሬም የተባለ ኤርትራዊ፣ ቃኘው ሠፈር ይኖር የነበረ ክርስቲያን ነው፡፡ ቤተሰቦቹ ሁለት መርዶ እንደመጣባቸው እየገለጡ ነው፡፡ በአንድ በኩል በአሰቃቂ ሁኔታ በአይሲስ መሠዋቱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ‹ሙስሊም› ነው መባሉ ነው፡፡
ኖርዌይ የነበሩ ኤርትራውያን ክርስቲያኖች ወዲያው ነበር ነገሩን የተቃወሙት፡፡ ነገር ግን አሥመራ ያሉት ቤተሰቦቹ እስኪረዱ ድረስ ትክክለኛ ስሙን ለመግለጥ አልተፈለገም፡፡ በዚህ መዘግየት የተነሣም ብዙ የፈጠራ ታሪኮች ተፈጠሩ፡፡
አንዳንድ የማኅበራዊ ሚዲያ አቀንቃኞች በላኩልኝ የውስጥ መልእክት የጀማልን ሙስሊምነት መካድ ሙስሊሞች ለክርስቲያኖች ያላቸውን ድጋፍና ፍቅር መካድ ነው ሲሉ ገልጠዋል፡፡ ለእኔ ግን ከተፈጠረው ‹ጀማል› ይልቅ እዚሁ አዲስ አበባ ያለው መሐመድ ካሣ ይህንን ልዩ ፍቅር ከንጋት ኮከብ በላይ አጉልቶ አሳይቶኛል፡፡ ልቡ እስኪደክም ኀዘንተኞቹን ለማጽናናትና ለመርዳት የሚደክመው፤ ለምን ጉባኤ አይደረግም፣ መዘምራን ለምን አይመጡም፣ መምህራን ለምን አያስተምሩም እያለ ልቅሶ ቤቶቹን ከክርስቲያኖቹ በላይ ሲያገለግል የነበረው፤ ተዝካራቸው መውጣት አለበት ብሎ ከካህናቱ ጋር የሚሟገተው፣ ድንበር ተሻጋሪውና ድልድይ ገንቢው መሐመድ ካሣ ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ፍቅር ከበቂ በላይ ማሳያዬ ነው፡፡
ያየሁት፣ የነካሁት፣ የበለጠኝ ማስረጃዬ፡፡ ፈጠራ አያስፈልገኝም፡፡
ኤፍሬም ሆይ በረከትህ ይደርብን፡፡

No comments:

Post a Comment