Monday, April 13, 2015

ስለጥርስ ቡርሻችን የማናውቃቸው አስገራሚ እውነታዎች

 እስኪ ስለጥርስ ቡርሻችን የማናውቃቸውን አስገራሚ እውነታዎችን  እናካፍላችሁ።
በእንግሊዝ የማንችስተር ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች እንደሚገልፁት የጥርስ ብሩሻችን በአማካኝ 100 ሚሊየን ለሚጠጉ ባክቴሪያዎች መጠለያ ነው።
አይጨነቁ ፣ በገዛ አፍዎ ሳይቀር ቁጥር ስፍር የሌላቸው ባክቴሪያዎች ይገኛሉ፥ እነዚህን ባክቴሪያዎች በጤናዎ ላይ ጉዳት እንዳያስከትሉ ማድረግ ይችላሉና።
አፋችን በየቀኑ ቁጥራቸው በርከት ያለ ባክቴሪያዎችን የሚያስተናግድ ሲሆን ፥ ጥርሳችንን ለማፅዳት የምንጠቀምበት የጥርሴ ቡርሽም የእነዚህ ባክቴሪያዎች ሰለባ ነው።
ይሁንና ጤናማ ያልሆነ  የባክቴሪያ መመጣጠን እስካለተከሰተ ድረስ ይህ ነው የሚባል ጉዳት በጤና ላይ ላያስከትል ይችላል ነው የሚሉት የህክምና ባለሙያዎች።
በተለይም የተራቀቁ የኤሌክትሮኒክ የጥር ቡርሾች እነዚህ ባኴቴሪያዎች ወደ ድዳችን ዘልቀው እንዲገቡ በማድረግ ጉዳትን ሊያስከትሉብን እንደሚችሉ ነው በኦክላህማ ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ማዕከል የጥርስ ህክምና ዶክተር እና ፓቶሎጂስት ፕሮፌሰር ቶማስ ግላስ የሚናገሩት።
በአፍ ውስጥ የሚገኙ ጀርሞች ያን ያህል ጉዳት ባያስከትሉም የጥርስ ቡርሽን በጋራ የመጠቀም ሁኔታ ካለ ግን የጀርሞች ስርጭትን በእጥፍ ስለሚጨምረው ጉዳት ያስከትላል።
ምንም እንኳን በጀርም እና ባክቴሪያ በተሞላው በጥርስ ቡርሻችን ምክንያት የአፍ ውስጥ ኢንፌክሽን ላይከሰትብን ይችላል፥ ሆኖም የጥርስ ቡርሻችን እና የምናኖርበት ቦታ ንፁህ መሆኑን ማረጋገጥ ግን ተገቢ ነው።
የጥርስ ብሩሻችን የበሽታ ምንጭ እንዳይሆንብን
1.በተቻለ መጠን መክደኛ እንዲኖረው ማድረግ ፣
2.የጥርስ ቡርሻችንን መክደኛን በየጊዜው ማፅዳት
3.ጥርሳችንን የምናፀዳበት መታጠቢያ (ሲንክ ) ከመፀዳጃ ቤታችን ርቀት ሊኖረው ይገባል፥ ምክንያቱም ውሃ በሚናፈስበት (ፍላሽ በምናደርግበት ጊዜ) ባክቴሪያዎች ወደ አየር ከመበተን አልፈው የጥርስ ቡርሻችን ላይ ሊሰፍሩ ስለሚችሉ፣
4.ፀረባክቴሪያ ያላቸውን የጥርስ ቡርሾችን መጠቀም፣
5.የጥርስ ቡርሻችንን ከሶስት እስከ አራት ወራተ ብቻ ተጠቅመን በአዲስ መተካት፣
ከመጠን ያለፈ የባክቴሪያ መጠን በአፋችን ውስጥ መገኘት ለድድ መድማት፣ ለጥርስ ህመም እና ለመጥፎ የአፍ ጠረን መከሰት ምክንያት በመሆኑ ለጥርስ ቡርሻችን ጥንቃቄ በመቸር ከእነዚህ መጠበቅ እንችላለን።


ተተርጉሞ የተጫነው፦ በሳሙኤል ዳኛቸው

No comments:

Post a Comment