Tuesday, April 21, 2015

ሰበር ዜና – ቅ/ሲኖዶስ ከነገ ሚያዝያ ፲፬ ቀን ጀምሮ የሰባት ቀናት ጸሎተ ምሕላ ዐወጀ፤ ቤተሰቦች የተሠው ክርስቲያኖችን ፎቶ፣ ስመ ክርስትና እና ሙሉ አድራሻ እንዲያቀርቡ አዘዘ – ‹‹ልጆቻችን የሃይማኖት ሰማዕትነትን የተቀበሉ የሃይማኖት መስተጋድላን ናቸው››










pat mat





  • ቅዱስ ሲኖዶስ ‹‹ግፉዓን ይትመሰጥዋ ለመንግሥተ ሰማያት፤ በሃይማኖታቸው ምክንያት ግፍ የሚደርስባቸው መንግሥተ ሰማያትን ይናጠቋታል››(ማቴ.11÷12) በሚል ርእስ በሰሜን አፍሪቃ ሊቢያ ውስጥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ የተፈጸመው የግድያ ወንጀልን በተመለከተ ዛሬ፣ ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀትር ላይ በድጋሚ በሰጠው ወቅታዊ መግለጫው፡- በግፍ የተሠውት ክርስቲያኖች፣ ሃይማኖታችንን አንክድም በማለት የሃይማኖት ሰማዕትነትን የተቀበሉ የሃይማኖት መስተጋድላን መኾናቸውን አረጋገጠ፤ ቤተሰቦቻቸውንም አጽናና፡፡
Qirqos parents and relatives mourns‹‹የመዋች ቤተሰቦች የኾናችሁ ወገኖቻችን ኹሉ፡-
በዚኽ ግፍ የተሞላበት ጭካኔ የጠገደሉት ልጆቻችን በዚኽ ዓለም የመኖር መብታቸው በአጭሩ ቢቀጭም ጌታችን፣ ‹‹የተገፉ መንግሥተ ሰማያትን ይናጠቋታል ማለትም ይወርሷታል›› ባለው አምላካዊ ቃለ እግዚአብሔር፣ ዕንባቸው አብሶ በመንግሥቱ የሚቀበላቸው መኾናቸውን ዐውቃችኹ፤
እንደዚኹም ልጆቻችን ‹‹ወኩን መሃይምነ እስከ ለሞት ወእሁበከ አክሊለ ሕይወት፤ እስከ ሞት ድረስ የታመንኽ ኹን፤ የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለኹ፤››(ራእይ 2÷10) ያለውን የጌታችንን ቃል ጠብቀው ሃይማኖታችንን አንክድም በማለት በሃይማኖት ሰማዕትነትን የተቀበሉ የሃይማኖት መስተጋድላን ስለኾኑ የጀግና እናት አታለቅስም እንደተባለው የልጆቻችኹ ሰማዕትነት በእግዚአብሔር መንግሥት ታላቅ ዋጋ ስላላቸው በዚኽ ከሐዘናችኹ እንድትጽናኑ ቤተ ክርስቲያን ታሳስባለች፡፡››
  • ነገ÷ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ መላው የአዲስ አበባ ገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንት፣ ካህናት እና የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች እንዲኹም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ሓላፊዎች እና ልዩ ልዩ ሠራተኞች በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎተ ፍትሐት እና ጸሎተ ወንጌል ይከናወናል – ‹‹ከነገ ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ለ7 ቀናት ያኽል በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ባሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት በግፍ ለተገደሉት ወገኖች ጸሎተ ፍትሐት፤ ለሀገራችን እና በአጠቃላይ ለዓለሙ ኹሉ ሰላም መጠበቅ፣ ለሰው ልጆች በሕይወት የመኖር መብት መከበር ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኖአል፡፡››
  •  በየትኛውም አካባቢ የሚገኙትን ወገኖቻችንን እና የቤተ ክርስቲያን ልጆችን ከመሰል ጥቃት ለመታደግ እንዲቻል ከመንግሥት ጋራ በቅርበት የሚሠራ ዐቢይ ኮሚቴ በቅዱስ ሲኖዶስ ይቋቋማል፡፡ 
  • ሥነ ሥርዐቱ በደቡብ አፍሪቃ በግፍ የተገደሉ ንጹሐን ኢትዮጵያውያንንም ይጨምራል፡source : /haratewahido.wordpress.com/

No comments:

Post a Comment