Tuesday, April 21, 2015

በኢራቅ በተፈፀመ የዓየር ጥቃት የአይ ኤስ መሪ ባግዳዲ ክፉኛ መቁሰሉ ተነገረ


በምእራባዊ ኢራቅ በተፈፀመ የዓየር ጥቃት የአይ ኤስ መሪ አቡ በከር አል ባግዳዲ ክፉኛ  መቁሰሉ ተነገረ።
ከአሸባሪ ቡድኑ  ጋር ንኪኪ ያላቸው ወገኖች ለዘጋርዲያን እንደተናገሩት፥ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በምእራባዊ ኢራቅ በዩናይትድ ስቴትስ መራሹ የዓየር ጥቃት ዘመቻ ጉዳት ደርሶበታል።

የአሸባሪ ቡድኑ መሪ የደረሰበት ጉዳት የከፋ ቢሆንም እስካሁን በህይወት እንዳለ ተገልጿል።

ሆኖም የቡድኑን የእለት ተእለት  እንቅስቃሴ ወደ መምራት አልተመለሰም ተብሏል።

የአይ ሲ ስ መሪዎችም ዋና መሪያቸው  የደረሰበት ጉዳት የከፋ በመሆኑ የሚተካው ሰው ለመመርጥ ተሰብስበው እንደነበርም ዘ ጋርዲያን ዛሬ አስነብቧል።

ጉዳቱ  የደረሰበት በፈረንጆቹ መጋቢት 18 ቀን በሶሪያ  እና ኢራቅ ድንበር ላይ አል ባጅ በተባለ  ስፍራ  በተፈፀመ የዓየር ጥቃት እንደሆነ በዘገባው ተመልክቷል።
ሆኖም በሰዓቱ ጥቃት በተፈፀመባቸው ሶሰስ ተሽከርካሪዎች ውስጥ ባግዳዲ እንደነበር አልታወቀም ነው የተባለው።

ከቅርብ  ጊዜ ወዲህ በዩናይትድ ስቴትስ መሪነት እየተፈፀሙ ያሉ የዓየር ጥቃቶች ውጤታማ  እየሆኑ መምጣታቸው የተነገረ ሲሆን፥ ከአንድ ወር በፊት በተፈፀሙ የዓየር ጥቃቶች የባግዳዲ ምክትል እና  የአይ ኤስ ወታደራዊ መሪ ተገድለው ነበር።
ምንጭ፦ http://www.theguardian.com/

No comments:

Post a Comment