Saturday, March 28, 2015

እንቅልፍ በቶሎ እንዲወስደን ማደረግ ያለብን ዘዴዎች


ሌሊት በመኝታ ሰዓት እንቅልፍ ቶሎ የማይዘን ከሆነ የአሜሪካ ተመራማሪዎች ችገሮቹን ይቀርፋሉ ያሉትን ዘዴዎች እናካፍልዎ።
1.    ከመኝታ በፊት ቢያንስ ለ60 ደቂቃዎች ያክል ማረፍ፦ ቀኑን ሙሉ በስራ ተወጥረን ከዋልን ማታ ላይ በቀላሉ እንቅልፍ ስለማይወስደን ሁሌም ከመኝታ በፊት ለ60 ደቂቃዎች ያከል እራስን ማረጋጋ   ወይም እረፍት ማድረግ እንቅልፍ ቶሎ እንዲወስደን ከሚረዱን ዘዴዎች አንዱ ነው።
2.    ለብ ባለ ውሃ ገላን መታጠብ፦ ከመኝታ በፊት ለብ ባለ ውሃ ገላን መታጠብም በመኝታ ሰዓት እንቅልፍ ቶሎ  እንዲወስደን ያደርጋል ተብሏል።
      በሙቅ ውሃ ታጥበን ከመታጠቢያ ቤት ስንወጣ የተውነታችን ሙቀት ባንዴ እንዲቀንስ በማደረግ የእንቅልፍ ስሜት እንዲሰማን አድርጎ ለእንቅልፍ እጅ እንድንሰጥ ያደርገናል።
3.    ካልሲ አድርጎ መተኛት፦ ካልሲ አድርጎ መተኛትም እንቅልፍ ቶሎ እንዲይዘን ያደርጋል ይላሉ ተመራማሪዎቹ።
      ይህም ካልሲው እግራችንን እንዲሞቅ በማድረግ እንቅልፍ እንዲወስደን ያደርጋል ተብሏል።
4.    የእንቅልፍ ስሜተ እስኪሰማን ድረስ አልጋ ላይ አለመውጣት፦ የእንቅል ስሜት ሳይሰማን አልጋ ላይ ወጥተን መተኛት ብቻውን እንቅል በቶሎ እንዲይዘን አያደርግም።
       ስለዚህም ተክክለኛ የእንቅልፍ ስሜት ሲሰማን አልጋ ላይ ወጥተን የምንተኛ ከሆነ በቶሎ እንቅልፍ ይወስደናልም ተብሏል።
5.    እራስን ማረጋጋት፦ በስራ እና በተለያዩ ነገሮች ተወጥሮ የዋለ አዕእምሯችንን በመኝታ ሰዓት ሳይሆን ቀን ላይ መተግበር እንቅልፍ በቶሎ እንድይዘንም ይረዳናል ተብሏል።
6.    በመኝታ ሰዓት የእንቅልፍ አይዘኝም ስጋትን ማስወገድ፦ በመኝታ ሰዓት እንቅልፍ አይዘኝም ብለን ስጋት ከተፈጠረንብ ተኝቶ ከማሰብ ይልቅ ከአልጋችን ላይ ተነስተን የእንቅልፍ ስሜት እስኪሰማን በሌላ     ክፍል መቆት ይመከራል።
በተጨማሪም ከመኝታ በፊት አንቅልፍ አይዘኝም የሚለውን አስተሳሰብም ማስወገድ አለብ ብለዋል ተመራማሪዎቾ።
7.    የእጅ ወይም የግድግዳ ሰዓቶን ከአልጋዎ አካባቢ ማራቅ፦ በመኝታ ሰዓት ተኝተን ሰዓት የምንመለከት ከሆነ በራሳችን መንገድ እንቅክፍን እያባረርን ነው ይላሉ ተመራማሪዎቹ።      
       ለዚህም ሰዓታችንን ከመኝታችን አካባቢ ማራቅ ወይም ከእይታችን ውጭ ማስቀመጥ ቶሎ እንቅልፍ እንዲይዘን ያግዘናል።
8.    ወረቀት ላይ መጻፍ፦ ሃሳብ አስጨንቆን እንቅልፍ ከከለከለን በውስጣችን ያለውን ሃሳብ በወረቀት ላይ ማስፈር እንቅልፍ ቶሎ እንዲመጣ እና ያለ ሃሳብ እንድተኛም ይረዳናል ተብሏል።
ምንጭ፦ yahoo.com/health from FBC
በሙለታ መንገሻ

No comments:

Post a Comment