Friday, March 27, 2015

ለረጅም ሰዓት መቀመጥ የሚያስከትለው ጉዳት


ከረጅም የእግር ጉዞ አንዲሁም ለረጅም ጊዜ ስራን ቆመን ከሰራን በኋላ መቀመጥ እረፍት ለማድረግ የሚመከር ቢሆንም፥ ለረጅም ሰዓት መቀመጥ ግን ጤናችንን እንደሚያዛባ ጥናቶች ያመለክታሉ።
ለረጅም ሰዓት መቀመጥ ጡንቻን፣ አጥንታችን እና የአተነፋፈስ ስርዓታችን እንዲዛባ በማድረግ እንዲሁም አዕምሯችን በሚሰራው ስራ ላይ ትኩረት እንዳይሰጥ በማድረግ ነው ጤናችንን ያውካል ያሉት ተመራማሪዎቹ።
ለረጅም ሰዓት መቀመጥ፦
አዕምሯችንን እና የሰውነት አካልን ይጎዳል፦ ለረጅም ሰዓት በቢሮ ውስጥ ወይንም በቤታችን ሶፋ ላይ ኮምፒውተራችንን ለመጠቀም ለረጅም ሰዓት ተቀምጠን የምንውል ከሆነ የሰውነታችን እና የአዕምሯችን ጤናን ያውካል።
ስለዚህ በተቻለን አቅም መንቀሳቀስ እና የቁም ጠረጴዛዎችን በመጠቀም ቆመን መስራት ይመከራል።
የጀርባ አጥንታችንን / spinal cord/ ይጎዳል፦ ለረጅም ሰዓት የምንቀመጥ ከሆነ የጀርባ አጥንታችን በቀላሉ ስለሚጎዳ ለጀርባ ህመም ሊያጋልጠን ይችላል።
የአተነፋፈስ ስርዓታችንን ያዛባል፦  ስፓይናል ኮርዳችን በመቀመጥ ብዛት ሊታጠፍ ስለሚችል ይህ ደግሞ ሳንባችን በቂ ቦታ እንዳያገኝ ያደርገዋል ይህም ሳንባችን በቀላሉ ለመታጠፍ እና ለመዘርጋት ነጻነትን ያጣል፥ ይህም ሳንባችን አየር እንደልቡ እንዳያስገባ እና እንዳያጠጣ በማገድ የአተነፋፈስ ስርዓታችንን ያዛባል።
በስራችን ላይ ትኩረትን እንድናጣ ያደርጋል፦ ሰውነታችን በቂ ኦክስጅን እንዳያገኝ በማድረግም የአእምሯችን ጤና ላይ ጉዳት ሊያስከትልም ይችላል ተብሏል።
ይህም በምንሰራው ስራ ላይ ትኩረት ሰጥተን እንዳንሰራ ያደርገናለም ተብሏል።
ስለዚህም ሙሉ ጤነኛ ለመሆን እና የምንሰራውን ስራ በትኩረት ለመስራት ያግዘን ዘንድም ስራችንን እየተንቀሳቀስን ወይንመ ቆመን መስራት ይመከራል።
የስራችን ጸባይ እና ሁኔታ ቆመን እንዳንሰራ የማይፈቅድ ከሆነም በቀን ውስጥ ለተወሰነ ደቂቃዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም ጥናቱ ያመለክታል።
ምንጭ፡ medicaldaily.com from FBC
የተተረጎመው እና የተጫነው፡ በሙለታ መንገሻ

No comments:

Post a Comment