Friday, May 8, 2015

ኢትዮጵያ ቡና ዳዊት እስጢፋኖስን በዲሲፕሊን ጉድለት ከክለቡ አሰናበተ


የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ዳዊት እስጢፋኖስን አሰናበተ።

ክለቡ ተጫዋቹ በተደጋጋሚ ባሳየው የዲሲፕሊን ጥሰት ምክንያት  ሊያሰናበተው እንደቻለም  ገልጿል።

ተጫዋቹ ምንም አይነት የጤና እክል ሳይገጥመው አሞኛል በሚል ሰበብ ለአንድ ሳምንት ከልምምድ መራቁ እና በህክምና ምርመራም ጤነኛ መሆኑ መረጋገጡን ክለቡ ከዲሲፕሊን ጥሰቶቹ መካከል ይጠቅሳል።

በተጨማሪም ተደራራቢ የዲሲፕሊን ጥሰቶችን ሲፈፅም መቆየቱን የጠቀሰው ክለቡ፥ ለተጫዋቹ የስንብት ደብዳቤ ሰጥቷል።

ከተጫዋቹ ጋር  ተይዞ የነበረውን ውልእና የውል አፈፃፀም  በተመለከተም ክለቡ እየመከረበት ይገኛል።

ዳዊት እስጢፋኖስ ክለቡ አሉኝ ከሚላቸው ተጫዋቾች እንደነበር  ይታወቃል።

በቶማስ ሰብስቤ
source ;FBC

No comments:

Post a Comment