Thursday, April 30, 2015

ቆንጆ ሴቶችን በሚገባ ለማፍቀር የሚያስችሉ 7ቱ ልዩ ልዩ የስህበት ህጎች



1. የምትፈልገውን እወቅ
በዓለም ላይ የብዙዎች ችግር የሚፈልጉትን አለማወቃቸው ነው፡፡ አንዳንዶች ደግሞ የሚፈልጉትን ለማወቅም ጭራሽ አይፈልጉም፡፡ ይህ በእርግጥ ግራ የሚያጋባ ጉዳይ ቢመስልም ፍቅርን በተመለከተ ግን በትክክል የምንፈልገውን ማወቅ ይጠበቅብናል፡፡ አንዳንዶቻችን በድንገት እንገናኛለን፤ ከዚም እንፋቀራለን፡፡ ወይም ደግሞ ያገኘነው ሁሉ ተቃራኒዎች እስከሆነ ድረስ ለመፋቀር ግድ የሌለን ሰዎች አንጠፋም፡፡ ይህ ትክክል አይደለም፡፡ በትክክለኛ ውስጣዊ ፍላጎታችን ላይ የተነጣጠረ የፆታ ምርጫ ሊኖረን ያስፈልጋል፡፡ እናም በትክክል የምንፈልገውን ለማወቅ ወሳኙ ጉዳይ ምን ምን አይነት ሰው ከእኛ ጋር እንደሚጣጣምና የበለጠ እንደሚመቸንም እራሳችንን መጠየቅ አለብን፡፡ ራሳችንን በመጠየቅ ውስጥ አዕምሯችን ትክክለኛ ምላሽን ያዘጋጅልናል፡፡ ጥያቄዎችህ በሚከተሉት መስፈርቶች ላይ ያነጣጥሩ፡-
– መልክ፣ ቁመና፣ ገቢ
– የአዕምሮ ንቃተ ህሊናና የፍጥነት ደረጃ
– የስራ የሙያ አይነት
– አለባበስ፣ ስብዕና
– ዘርና የትውልድ ሁኔታ፣ ሀይማኖት፣ የትምህርት ደረጃ
– ለፍቅራዊ አቀራረብና ለወሲብ ያላት የጋባዥነትና የመስብዕነት ደረጃ
ሌላው የምትፈልገውን በትክክል አውቀሃል ለማለት ፎቶግራፋዊ ምስሉ ምን እንደሚመስል በእጅህ ለመሳል ሞክር፡፡ እርግጥ ነው ስዕል መሳል ላይሆንልህ ይችላል፤ እኔም ዳቪንቺን እንዳልሆንክ እገምታለሁ፡፡ ይሁን እንጂ የልብህን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ስዕል ሳል፣ ቁመና፣ የመልክ ቅርፅ፣ ፀጉር፣ ወገብ፣ ዳሌ፣ አለባበስና የመሳሰሉ የምስል ገለፃዎችን በስዕሉ ላይ አስፈር፡፡ ይህን ስታደርግም የውስጥህን በትክክል ደፍቆ ማለት ነው፡፡ ከዚያም ከዚህች መሰል ሀሳባዊ ፍቅረኛህ ጋር የምትመሳሰል ሴት ከኢንተርኔት ውስጥ ግባና አውጣ፡፡ አውጣ ስልህ ግን ሌላ ሳይሆን ፎቶውን ፕሪንት አድርገው ወይም ፎቶ ቤት አሳጥበው ለማለት ነው፡፡ ይህ ፎቶ የአንተን ፍቅረኛ ማንነት የሚገልፅ ነው ማለት ነው፡፡ ይህን ፎቶ አንተ ልታየው በምትችልበት የተለያዩ ቦታዎች ላይ ለጥፈው፣ በሞባይልህ ውስጥ፣ በኮምፒውተርህ (Screen Saver)፡- በመኝታ ክፍልህ፣ በቦርሳህ ውስጥ፣ በቢሮህ ጠረጴዛ፣ በመኪናህ ውስጥ ወዘተ…
2. የፈለካትን ሴት እንደምታገኛት እመን
ይህ ዩኒቨርስ የአንተ ውስጣዊ የምናብ ዓለም እንጂ በራሱ አንተ እንደምታምነው እውን የሆነ አይደለም፡፡ ቅርፅ የምትሰጠው አንተ ነህ፡፡ ከአንተ ውጭ ያለው ዓለም ከአንተ ውስጥ ያለው ዓለም የፈጠረው ነፀብራቅ በመሆኑ ይህችን ከውስጥህ የቀረፅካትን ውብ ልጅ ደግሞ የማግኘት ዕድልህ በጣም ሰፊ ነው፡፡ ይህ ዓለም የአንተ እምነትና ቀረፃ ውጤት ነው፡፡ ቀረፃው ከሌለህ ምን እንደሚከሰት ልታምን ትችላለህ? በቅድሚያ የምትፈልገውን ቅርፅ አላየህምና፡፡ እንዲሁም ደግሞ የምትፈልገውን አውቀህ ካላመንክበት ዋጋ የለውም፡፡ አንድ ፊቱን የምትፈልገውን ባታውቅ ይሻላል፡፡ አንተ የሕይወትህ ሊዮናርዶ ዳቪንቺ ነህ፡፡ ፈጣሪ በዚህ ዓለም ላይ ያልተገደበ የፈጠራና የፈለከውን የማግኘት ስልጣን ሰጥቶሃል፡፡ እናም በዚህ ዓለም የፈለካትን ውብ ሴት የማግኘት 100% ዕድሉ አለህ፡፡ ይህ ግን የሚወሰነው በአንተ እምነት ውስጥ ነው፡፡ ይህ ዩኒቨርሲቲ የአንተ እምነት ተገዥ ነው፤ የፈለካትን ቆንጆ በትክክለኛ በ3 ዳይሜንሽን እስከ ቀረፅካት ድረስ አንተ ዝም ብለህ ለመቀበል ተዘጋጅ፡፡
3. የማመን መገለጫ መቀበል ነው
አንድ ነገር በትክክል እጃችን መግባቱን የምናውቀው ነገር ያው አራቱ ስሜት ህዋሳትን መሰረት ሲያረጋግጥ ነው፡፡ ነገሩን ከጨበጥነው፣ በዓይናችን ካየነው፣ ጠረኑን ካሸተትነው፣ እንዲሁም ድምፁን ከሰማነው ነገሩ በገሃድ ተከስቷል ወይም ደግሞ እጃችን ገብቷል እንላለን፡፡ ይህም ነገር እንዳለ ስለምናምን መቀበላችንን እናረጋግጣለን፡፡ ይህ በእርግጥ አይቶ ማመን እንጂ ሳያዩ ማመንን አያንፀባርቅም፡፡ ይህ ማመን ሳይሆን መጠራጠር ነው፡፡ ትክክለኛው እምነት በማይታየው ዓለም ውስጥ አንተ የምትፈልገው ነገር ሊከሰት እንደሚችል ማመን ብቻ ሳይሆን እንደተከሰተ ቆጥረህ መቀበልም መቻል አለብህ፡፡ የነገሮች ክስተት የሚጀምረው አዕምሮህ ውስጥ ነው፡፡ በአዕምሮህ ውስጥ የሌለው ክስተት ከውጪ ሊከሰት አይችልም፡፡ እናም የውጪውን ክስተት ሊያፋጥንልህ የሚችለው በአእምሮህ ውስጥ የምትፈልጋት ውብ ሴት ከአንተ ጋር በፍቅር ወይም በትዳር ውስጥ እንዳለች አድርገህ ክስተቱን መቀበል ስትችል ነው፡፡ ይህን ስታደርግ በትክክል ተቀብለሃታልና ውጫዊ ክስተቱም፣ ፈጣን ይሆንልሃል፡፡ ሙሉ እምነት ማለት ይህ ነው፡፡
4. በውስጥህ የፍቅር ስሜትን አሳድር
በኑሮህ ውስጥ ቆንጆይቱ ፍቅረኛ በትክክል መቀረጿንና መቀበልህን የምታረጋግጥበት ነገር ውስጣዊ ስሜትህ የደስ ደስ ፍቅር ሲሰማው ነው፡፡ ሁላችንም እንደሚገባን አንድ ከልባችን የምንፈልገው ነገር እጃችን ሲገባ በውስጣችን ከፍተኛ የደስታ ስሜት ይፈጠርብናል፡፡ በመሆኑም ውስጣዊ የደስታ ስሜት የማግኘታችንና ነገሩን የመቀበላችን ማረጋገጫ እስከሆነ ድረስ በአዕምሯችን ውስጥ በትክክል ውቧን ልጅ ተቀብለናታል ብለን ለማመን የደስታ ስሜት ሊሰማን ይገባል፡፡ ልክ የፈለካት ልጅ ጋር በጥሩ የፍቅርም ሆነ የትዳር ህይወት ውስጥ እንደተጣመርክ አድርገህ መቀበል ብቻ ሳይሆን በሚገባ መደሰትም ይኖርብሃል፡፡ ጥሩ የፍቅርና የደስታ ስሜት በተሰማህ ቁጥር ልጅቱን የማግኘት ዕድልህ በጣም ፈጣን ይሆናል፡፡ ይህ ዓለም በአንተ ውስጣዊ ስሜት ውስጥ በቀላሉ ተፅዕኖ ውስጥ የሚወድቅ በመሆኑ እንደ እምነትህ ይሆንልህ ዘንድ ውስጥህ በልጅቷ ደስ ይበለው፤ ይህም የደስደስና የፍቅር ስሜት ለተከታታይ ቀናት ከአንተ ጋር ይቆይ፡፡ የፍቅር ስሜት ሊይዘን የሚገባው ልጅቷ በገሃድ ከመጣችና ከተዋወቅን በኋላ መሆን የለበትም!
5. ቆንጆዎችን አጉልተው በሚያሳዩ ቦታዎች አዘውትር
እንደሚታወቀው ውበት ራሱን የቻለ ኢነርጂ ነው፡፡ በዓለም ላይ ሁለት አይነት ኢነርጂ አለ፤ ከፍተኛና ዝቅተኛ፡፡ የውብ ነገሮች ሞገድ በከፍተኛ ፍሪኩየንሲ ውስጥ ያርፋል፡፡ በውበት የማይታዩ ደብዛዛ ነገሮች ደግሞ በዝቅተኛ ፍሪኩየንሲ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የአንተ ኃላፊነት ውቦች የሚገኙበት ፍሪኩየንሲ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ ውብ መኖሪያ አካባቢዎች፣ መ/ቤቶች፣ መዝናኛ ቦታዎች፣ ሱፐር ማርኬቶች፣ ሪዞርቶች፣ ህንፃዎች፣ ሆቴሎችና የመሳሰሉ ቦታዎች ቆነጃጅትን እንደንብ የሚስቡ ቦታዎች ናቸው፡፡ ጠላትን ለማጥቃት ማነጣጠር ያለብህ ጠላት ከሚያርፍበትና ከሚኖሩበት ቦታ እንደሆነ ሁሉ ቆንጆዎችንም ለማጥመድ ወደነዚህ አካባቢዎች ከመምጣት መቦዘን የለብህም፡፡ በእርግጥ ቆንጆ ሲባል መልክ ብቻ እንዳይመስለህ፤ ትልቁ ውበት ውስጣዊውና በደስ ደስ የተመላው ስሜትና ስብዕና ጭምር ነው፡፡ ዝቅተኛ ፍሪኩየንሲ ባላቸው ቦታዎች ውስጥ መልካቸው ያማሩ ሰዎችን ልታገኝ ትችላለህ፡፡ ነገር ግን በዝቅተኛ ፍሪኩየንሲ ውስጥ የሚኖረው ስሜት ዝቅተኛና ደብዛዛ ነው፡፡
6. ፍላጎትህን በንግግር አረጋግጠው
ይህ እንግዲህ ከፍተኛው የእምነትህ ሀይል መንፀባረቂያ ነው፡፡ ‹‹ቃል ሥጋ ሆነ›› እንደሚለው መፅሐፉ የአንተም ገንቢ ቃላቶች ፍላጎትህን ወደ አካላዊ ክስተት የመቀየር አቅማቸው ከፍተኛ ነው፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን ንግግሮች በተደጋጋሚ አንብባቸው፤ በንግግርህ ውስጥህም እንዳስፈላጊነቱ እያስገባህ ተጠቀምባቸው፡-
1. እኔ ለቆንጆ ሴት የተፈጠርኩ ነኝ
2. ቆንጆዎች የተፈጠሩት ለእኔ ነው
3. ቆንጆ በማፍቀሬ እጅግ ደስተኛ ነኝ
4. ፈጣሪዬ ቆንጆ አፍቃሪ ስለሰጠኝ ከልብ አመሰግነዋለሁ
5. እኔ ለቆንጆ ሴት የተመቸሁ ሰው ነኝ
6. አበቦች ንቦችን እንደሚስቡ ሁሉ እኔም ቆንጆዎችን የመሳብ ሀይል አለኝ፡፡
7. ቆንጆ ማፍቀር እችላለሁ፤ መብቴም ነው
8. ይህ ዩኒቨርስ የፈለኩትን ቆንጆ ስለሰጠኝ አመሰግነዋለሁ፡፡
9. በዚህ ዓለም ውስጥ እጅግ ብዙ ቆንጆዎች አሉ
10. ውስጤ በቆንጆ ልጅ ፍቅር ተሞልቷል!
7. ደካማ ጎናቸውን እወቅ
እንደሚታወቀው የትኛውም አይነት መስተጋብር በችግር ወይም በክፍተት ውስጥ የሚፈጠር ነው፡፡ ነጋዴና ደንበኛን የሚያስተሳስረው የሁለቱም ችግርና ድክመት ነው፡፡ ነጋዴው ከደንበኛው ገንዘብ ይፈልጋል፤ ደንበኛው ደግሞ የጎደለውን ለመሙላት አገልግሎትና የምርት ውጤት ከነጋዴው ይፈልጋል፡፡ ይሁን እንጂ ሁለቱም ሙሉ ከሆኑና የጎደላቸው ከሌለ ነጋዴውም ሆነ ደንበኛው ሊገናኙ አይችሉም፡፡ ባልና ሚስትን የሚያስተሳስራቸው ነገር ቢኖር ሌላ ጉዳይ አይደለም፤ የሁለቱም ድክመት ነው፡፡ ሴቷ ያላትን ድክመት በወንዱ ጠንካራ ጎን ለመሸፈን ስትል ወንዱን ትፈልገዋለች፤ ወንዱ ያለውን ደካማ ጎን ደግሞ እሱ በሌለው ነገር ግን ሴቷ ባላት ጠንካራ ጎን ለመሸፈን ስለሚፈልግ ሴቷን ይፈልጋታል፡፡ ነገር ግን ሁለቱም ደካማ ጎን ከሌላቸው ወይም ደግሞ አንዱ የሌላውን ደካማ ጎን መሙላት የማይችል ከሆነ ትዳሩ አይመሰረትም፤ ሁለቱም ፆታዎች ከትውውቅ የዘለለ ፍቅር ሊኖራቸው አይችልም፡፡
በመሆኑም ፍቅር ሊመሰረት የሚችለውም ሆነ ቆንጆዋ እንስት ወዳንተ ልትመጣና ከአንተ ጋር ልትቆይ የምትችለው አንድ ወይም ከአንድ በላይ ችግሮች ወይም ደካማ ጎኖች ወይም አስጊ ጉዳዮች ሲኖራት ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም በትክክል የምታስፈልግህን ሴት ለማወቅ በቅድሚያ የአንተ ደካማ ጎኖች፣ ችግሮችና ስጋቶች ምን ምን እንደሆኑና እነዚህን የባህሪ ድክመቶችና ስጋቶችም ምን አይነት ባህሪ ያላት ሴት ልትሸፈንልህ እንደምትችል አስብ፡፡ እንዲሁም በትክክል የምትፈልጋት ሴት የትኛዋ ልትሆን እንደምትችል ለማወቅ ደግሞ የሴቷን ደካማ ጎኖች በሚገባ ማወቅና አንተም ይህን ለመሙላት የሚያስችሉህ ጠንካራ ጎኖች በሚገባ እንዳሉህ ለማወቅ ሞክር፡፡ ይህ እንግዲህ ‹SWOT analysis› ወደሚለው ፅንሰ ሀሳብ ይወስደናል፡፡
‹SWOT analysis› ለአንተ፣
‹SWOT analysis› ለእሷ፣
(‹SWOT› Means “S=Strength, (ጠንካራ ጎኖች)፣ W=Weakness (ደካማ ጎን)፣ O=Opportunity (መልካም ዕድሎች)፣ T=Threat” (አስጊ ጉዳዮች) የሚሰኙ ናቸው፡፡ በዚህ መልክ ከተነተንክ በኋላ ወደማማለሉ ቀጥል፡፡ ካማለልካት በኋላም በሚገባ ልታቆያት እንደምትችል ማወቅ ትችላለህ፡፡ የእሷ ጥንካሬዎች የአንተን ደካማ ጎኖች የሚሞሉ መሆን አለባቸው፤ የአንተ ጥንካሬዎች አደግሞ የእሷን ደካማ ጎኖች የሚሞሉ መሆን አለባቸው፡፡ 
source  : http://www.zehabesha.com/

No comments:

Post a Comment