Tuesday, April 14, 2015

ለ73 አመታት በትዳር የዘለቁት ጥንዶች በሁለት ደቂቃ ልዩነት ይህችን አለም ተሰናብተዋል

ለ73 አመታት በትዳር የዘለቁት ጥንዶች በሁለት ደቂቃ ልዩነት ይህችን አለም ተሰናብተዋል
 ልብወለዳዊው የእነ ሰብለ ወንጌልና በዛብህ እስከ መቃብር የዘለቀ ፍቅር በአሜሪካ እውን ሆኗል ይላል የሜትሮ ዘገባ።
ለ73 አመታት በትዳር የኖሩት ጥንዶች በሁለት ደቂቃ ልዩነት ውስጥ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
ወንድየው ዊሊያም ዊልሰን ይባላሉ፤ 93 አመታቸው ነበር።
ባለቤታቸው ደግሞ የ89 አመታቸውን ልደት አክብረዋል።
ጥንዶቹ በልጅነታቸው በትምህርት ቤት ውስጥ በአትሌቲክስ ስፖርት ሲሳተፉ ነበር የተገናኙት። 
በትምህርት ቤት የተመሰረተው የፍቅር ግንኙነት ወደ ትዳር አምርቶም ለ73 አመታት የትዳር ህይዎት አሳልፈዋል።
ጥንዶቹ የአልዛይመር ህመም ተጠቂዎች የነበሩ ሲሆን ሰሞኑን አሜሪካ ኬንቱኪ ውስጥ በሁለት ደቂቃዎች ልዩነት ይህችን አለም መሰናበታቸው ተገልጿል።
from: FBC
ምንጭ፦ http://metro.co.uk

No comments:

Post a Comment