Wednesday, April 1, 2015

ሴት ልጅ እንዳፈቀረችህ ማረጋገጥ የምትችልባቸው 10 መንገዶች የቅርብ ጊዜ የስነ ልቦና ጥናታዊ ሪፖርቶች


ለአንተ ልዩ ፍቅርና መውደድ እንዳላትና እንደሌላት አዕምሮዋን በአካላዊ
እንቅስቃሴዎቿ በኩል በቀላሉ እንድታነብ ያስችሉሃል!! አካላዊ እንቅስቃሴዎች ዋነኛዎቹ
የመግባቢያ መንገዶች ናቸው፡፡ እነዚህ እንቅስቃሴዎች ግልፅ አካላዊ እንቅስቃሴና
ዝግ አካላዊ እንቅስቃሴ ይባላሉ፡፡ አካላዊ እንቅስቃሴዎች በራሳቸው ቋንቋ በመሆን
ከንግግርም በላይ በሆነ መልኩ መልዕክት ያስተላልፋሉ፡፡ እንዲህ አይነት ተግባቦት
በአብዛኛው በተቃራ ፆታ ግንኙነት ውስጥ በተለይም በሴቶች ላይ ይስተዋላሉ፡፡ ግልፅ አካላዊ
እንቅስቃሴ አንድ ጊዜ ከሴት ጋር አይን ለአይን ከተገጣጠምክ ፊቷን ካዞረች በኋላ ያላትንም እንቅስቃሴዎች አስተውል፡፡ አይናች በመጋጨቱ አፍረት ወይም መጨናነቅ ነገር
ከታየበት ተመችተሃታል ወይም ወዳሃለች ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ፀጉሯን
እንደማፍተልተል፣ ልብሷን ወይም ጌጣጌጧን ማስተካከል ወይም ደግሞ እጇ ላይ ባለው ነገር መጫወት ከጀመረች እነዚህ ግልፅ የሆኑ  ማረጋገጫዎችህ ናቸው፡፡ - ውስጥ እጇን
አንብብላት፡- በአጋጣሚዎች እና አንድ ላይ በምትሆኑባቸው ሁኔታዎች ውስጥ እጇን
ብትመለከት እሷም አሳልፋ ውስጥ እጇንና የእጇን አንጓ እንድትነካ ከፈቀደችልህ ሌላው ያንተ እሷን የመመቸት የአዕምሮ ፍቃድ ማሳያ አንዱ መንገድ ነው፡፡ ይህም ሁኔታ ‹‹ከፈለከኝ
ያንተው ነኝ›› እንደማለት ነው፡፡ -
 ማጎንበስ፡- በምታጎነብስበት ጊዜ ትከሻዋን ወደ አንተ
በመስበቅ ካጎነበሰች ዕድል በእጅህ ገብታለች
ማለት ነው፡፡ - እግሮቿን ከፍታ በምትቀመጥባቸው አጋጣሚዎች ካሉ አንተ
ጋር በመሆኗ ምቾት ተሰምቷታል ማለት ነው፡፡
- አንድ ሴት አንድን ሰው በምታይበት ጊዜ
የአይን ብሌኗ ከሰፋ ያንን ሰው እንደምትወደው
በተቃራኒው ደግሞ የአይን ብሌኗን ካጠበበች
ለዛ ሰው ጥሩ ስሜት እንደሌላት አንድ መገለጫ ነው፡፡ አይን ለአይን በምትጋጩበት
ጊዜ ፈገግታን ከቸረችህ ወደ እሷ ሂድና
አነጋግራት፡፡ ሌላው እንደ መልካም ነገር
መገለጫ የሚወሰደው አንተ በምታወራበት
ጊዜ ለረባ ባልረባው ፈገግ የምትል ወይም ሳቅ
የምታበዛ ከሆነ በእርግጠኝነት በደንብ ተመችተሃታል ይሄ ደግሞ የበለጠ የተሻለ ነው፡፡
- በምታወሩበት ጊዜ ሁሉ በተለይ ደግሞ እሷ
ስታወራ አንተን በተለያዩ አጋጣሚዎች
የምትነካህ ከሆነ መልካም ነገር አለ ማለት
ነው፡፡ አይኖቻችሁ በሚጋጠሙበት ጊዜም
ምቾት የማይሰጥ ቢሆን እንኳን እንደተፋጠጣችሁ ልትቆዩ ትችላላችሁ፡፡ በዚህ
አጋጣሚ ላይ መርሳት የሌለብህ ነገር ቢኖር
ፊትህን ከማዞርህ በፊት ፈገግ ማለትን ነው፡፡
ይህ ሁኔታ ታዲያ የአንተ እሷን መውደድና
መልካም ሰውነት ያሳያል፡፡ ከዚህ
በመቀጠልም በአንዳንድ አጋጣሚዎች እየሰረቀቸፍ ስታይህ ልታጋጥምህ ትችላለች፡፡
ከሁለተኛውና ከሶስተኛው መገጣጠም በኋላ
እንድታናግራት መፈለጓን እርግጠኛ መሆን
ትችላለህ፡፡ እንደ መልካም ተጫዋችነትህ
የጨዋታውን ህግ በማክበር የፈለገችውን ነገር
ማሟላት ግድ ይልሃል፡፡ መሽከርከር፡- አንድ ሴት ፀጉሯን አየር ላይ ወርውራ ወዲያው ዞራ
ካየችህ አንተ እንድታያት ለማድረግ እየጣረች
መሆኑን ማመን ትችላለህ፡፡ ዝግ አካላዊ
እንቅስቃሴዎች በማንኛውም ሁኔታ
ስትመለከታት አይኗን ውስጡን
የምታሽከረክረው ከሆነ በአንተ አቀራረብ ማፈሯንና እንዲሁም በአንተ ደስተኛ
አለመሆኗን ለሰዎች ለማሳየት እየጣረች
መሆኑን ማወቅ አለብህ፡፡ ይህ ነገር ከተፈጠረ
እሷን የማግኘት እድልህ ትንሽ በመሆኑ
ማድረግ ያለብህ ፊትህን አዙሮ መሄድ ነው፡፡ -
በምታወሩበት ጊዜ እጇን ካጣመረች መጨናነቋን ወይም በሁኔታው ምቾት
እንዳልተሰማትአመላካች በመሆኑ
እስትራቴጂህን ወይም ስልትህን በፍጥነት
መቀየር ይኖርብሃል፡፡ ሌላው ከዚሁ
ከማጣመር ጎን የሚያያዘው የእግር ማጣመር
ነው፡፡ እግር ማጣመር ልክ እጅን የማታመር ያህል መጥፎ ሲሆን ይህን አጋጣሚ የበለጠ
መጥፎ የሚያደርገው ደግሞ አንድ ጊዜ እግሯን
ካጣመረች እጇንም የማጣመር ሁኔታ ከፍተኛ
መሆኑ ነው፡፡ ይሁንና እግሯን አጣምራም
ቢሆን ጉልበቶቿ ወደ አንተ ከዞሩ ትንሽ
ከመጨነቋ ውጪ ከአንተ ላይ ፍላጎት እንዳላት ያመላክታል፡፡ ተቃራኒው
ሆኖ ጉልበቷ በሌላ አቅጣጫ ከዞረ ግን ችግር
ውስጥ ነህ ማለት ነው፡፡ ወደኋላ መሸሽ ወይም
መለጠጥ፡- ወንበር ላይ ከአንተ ራቅ ብላ
ወይም ተለጥጣ የምትቀመጥ ከመሆን በደንብ
የሚስተዋል አንተን ያለመሻቷ መገለጫ ነው፡፡ ስለዚህ የእኔ ምክር የሚሆነው የዚህ አይነት
አካላዊ እንቅስቃሴዎችን በምታይበት
አጋጣሚ ጨዋታውን ጥሎ መውጣት ብቻ ነው
መፍትሄ የሚሆነው በእንደዚህ አይነት አጋጣሚ
ሴቷን የራሳቸው ማድረግ የሚችሉት ልምዱ
ያላቸው ብቻ ናቸው፡፡ የአካላዊ እንቅስቃሴ ማታለያዎች አንድ ሴት አንተን እየተከታተለችህ
መሆኑንና ያለመሆኑን ለማወቅ አንድ
የሚያስቅና የሚሰራ ማታለያ ልንገርህ፡፡ እሷ
አንተን በምታይበት ሁኔታ ላይ ሆነህ ሰዓትህን
እያየህ በዝግታ ከ1-3 ቁጠርና ቀና ብለህ
እያት፡፡ እሷም ሰዓቷን እያየች ከሆነ አንተን ስታይህ እንደነበር እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡
ይህ ተፈጥሯዊ የሆነ አንተን የሚወድ ሰው
ባህሪ ነው፡፡ ልክ አንተ ሰዓትህን ማየት
ስትጀምር እሷም ምን እየጠበክ እንደሆነ
በማሰብ ሰዓቷን ታያለች፡፡ ተጨማሪ የአካላዊ
እንቅስቃሴ መረጃዎች 1. ፀጉር ማፍተልተል አብዛኛውን ጊዜ ፀጉሯን የምታስተካክል
ወይም የምታፍተለትል ሴት የወንዶችን አይን
ለመማረክ የምትሞክረው ናት፡፡ ፀጉር
ማፍተልተሏንም ሆነ መነካካቷን በደቂቃ
ውስጥ ሶስት ጊዜ የምታደርገው ከሆነ
መያዝም ሆነ መታየትን የምትፈልግ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡ ሌላው ደግሞ
ፀጉሯንየምትነካበት መንገድም የራሱ የሆነ
መልዕክት እንዳለው መዘንጋት የለብህም፡፡
ይህም ፀጉሯን በቀስታ የምትነካካ ከሆነ
የፍቅር ጥበብ እንዳላት ማወቅ የምትችል
ሲሆን ከፈጠነች ደግሞ ማፈሯንና ትዕግስት አልባ መሆኗን ማየት ትችላለህ፡፡ 2.
የብርጭቆ ጠርዝ ላይ እጅን ማሽከርከር
በሲግመንድ ፎርይድ ቲዎሪ መሰረት ይህ
ምልክት ለወሲብ የመጋበዝ ያህል ነው፡፡ ይህ
አባባል ታዲያ በብዙ ሴቶች ተደግፏል፡፡ ይህን
ጊዜ ታዲያ የጣቶቿን እንቅስቃሴ ልብ ማለት አለብህ፡፡ በዝግታ ጣቶቿን የምታሽከረክር
ወይም የምታንቀሳቅስ ከሆነ ጥልቅ የሆነ
እርጋታን፣ እራስ መቆጣጠርንና ጥበቃን
አመላካች ስለሆነ ከጎኗ ልትቀመጥ ትችላለህ፡፡
በሌላ መልኩ ደግሞ በጥፍሯ ብርጭቆውን
መምታት ከጀመረች ለነገሮች ትዕግስት ማጣቷንና
መቸኮልን ወይም በሌላ መልኩ በወንድ
ጓደኛዋ መናደዷን አመላካች ነው፡፡ 3. በክንዷ
ስትደገፍ አሪስቶትል እንዳለው ከሆነ የሴት እጅ
ብዙ ነገር ያወራል፡፡ በአካል እንቅስቃሴ ላይ
ጥናት አድራጊዎች ደግሞ ሴቶች በእንቅስቃሴያቸው የበለጠ ነገሮችን
እንደሚገልፁ ያብራራሉ፡፡ በክንዷ ደገፍ ብላ
እጇን አገጯ ስር በማስቀመጥ አይኗ በሀሳብ
ከዋለለ ተመስጣብኛለች ብለህ በማሰብ
እንዳትሳሳት እንደውም በዛ ሰዓት ላይ እራሷን
በመጠየቅ ላይ ስለምትገኝ ትንሽ ታገሳት፡፡ እሷም በዛ ሰዓት እያሰበች ከምትሆናቸው
ጥያቄዎች አንዱ ‹‹ለዚህ ሰው እገባዋለሁ?››
ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ሴቶች ብዙ ጊዜ
ለጥያቄዎቻቸው መልስ የሚፈልጉት በዚህ
መልኩ ስለሆነ ነው፡፡ መልሱ ምን እንደሆነ
አንተ ታውቀዋለህ፡፡ ስለዚህ በተሳካ ሁኔታ እረጋ በማለትና በቀልድ በማዋዛት ውሳኔዋን
ልታስቀይራት ትችላለህ፡፡ 4. እጇን በማጣመር
ተደግፋ ስትቀመጥ ይህ አጋጣሚ በጭፈራ
ቤትም ሆነ በየትኛውም ቦታ ሴት በማደን ላይ
ከሆንክና ካጋጠመህ ዕድለኛ አይደለህም ማለት
ነው፡፡ በዚህ አይነት አጋጣሚ ያለች ሴት ሁኔታህ አልተመቻትም ወይም
አልተማመነችብህም ማለት ነው፡፡ ይህ ሲሆን
ታዲያ የተዘጋጀህበትም ቀልድም ሆነ ፈርጣማ
ሰውነትህ ትርጉም ስለሌላቸው ባትለፋ
ይሻላል፡፡ አይ ካልክ ደግሞ ቀለል ያለ የወሬ
መጀመሪያ መንገድ ብትፈልግ ያዋጣሃል፡፡ 5. ከንፈሯን ስታረጥብ አንድ ሴት ከአንተ ጋር
እያወራች በተደጋጋሚ ከንፈሯን የምታረጥብ
ከሆነ ለፍቅር ያላትን ተነሳሽነት ይገልፃል፡፡
የስነ ባህል ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ
ሴቶች እንደዚህ
አይነት ምልክት የሚሰጡት ከንፈራቸው ላይ ሌላ ነገር እንዲቀመጥ ሲፈልጉ ነው፡፡ ምን
ሊፈልጉ እንደሚችሉ መቼም ላንተ መንገር
የለብኝም፡፡ 6. ሽፋሽፍቶቿን የምትነካካ
ሽፋሽፍቶቿን የምትነካካ ከሆነ ነፃነት ያላት ሴት
መሆኗን መናገር ይቻላል፡፡ በዚህ አጋጣሚ
ውስጥ መቀለድም ሆነ በትልቁ መሳቅ ላይጠበቅብህ ይችላል፡፡ ተነሳሽነቱን እሷ
መውሰዷ ካልደበረህ በሁኔታዎቹ አብራችሁ
ልትዝናኑ ትችላላችሁ፡፡ 7. እግር ማወዛወዝ
እግር ማወዛወዝም ሆነ በፍጥነት ማጣጠፍ
ሴቷ ለወሲብ ያላትን ተነሳሽነት ያሳያል፡፡ ይህን
አጋጣሚ ደግሞ የበለጠ የሚያበረታታው እግሯን በማንቀሳቀስ ላይ
እያለች ሳታስበው የምትከፍት ከሆነ ነው፡፡
በሲግመንድ ፎርይድ ክላሲካል ቲዮሪ መሰረት
ይህ አጋጣሚ ለወሲብም ክፍት መሆኗን
ጠቋሚ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ
ሳይነሳ የማይታለፈው የምታደርገው የጫማ አይነት ነው፡፡ የጫማው አይነት ለማውለቅ
የበለጠ ቀለል ያለ ከሆነ ለነገሮች ያላትም
ተነሳሽነት ቀላል መሆኑን የበለጠ አመላካች
ነው፡፡ ለዚህ እንደ ምሳሌ የሚጠቀሰው
በቤዚክ ኢንስትኒክት /Basic Instinct/
ፊልም ላይ የሻሮን ስቶን እግር አከፋፈት ነው፡፡ 8. የጣቶች አይነት አንድ ሴት ለእጇ ያላት
አመለካከት የበለጠ ነገሮችንገላጭ ሲሆን
በደንብ የተሰሩ ረጃጅም ጣቶች በጥንቃቄ
የተቀለሙ ጥፍሮች መልካም የሆኑ አነቃቂ
ነገሮች ናቸው፡፡ ይሁንና ሴቷ እጆቿን
የምታንቀሳቅስበት መንገድ የበለጠ ጥንቃቄ ሊደረግበት የሚገባው ነው፡፡ ለረጅም ሰዓት
እጆቿ ላይ በመፍጠጥ ከቆየች መናደዷን
መረዳት ትችላለህ /ምናልባት ባንተ?/
ጠረጴዛውንም በጥፍሮቿ የምትመታ ከሆነ
ተመሳሳይ መልዕክት ስለያዘ ብታስብበት
ይሻላል፡፡ 9. ከንፈሯን ከበላች በመሳሳም ወቅት ከንፈርህን ከነከሰችህ ፍፁም
አታቋርጣት፡፡ ምንም መጥፎ የሆነ ነገረ
የለም፡፡ ግን እሷ በራሷ የራሷን የምትነክስ
ከሆነ ለመጨናነቋ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
ለምን? ለሚለው መልስ ምናልባት በጥያቄ
አይን አፍጥጠህባት ይሆን? 10. ነፍሷን አዳምጠው እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ
መደበኛ ወንድና ሴት ግንኙነት ውስጥ ያሉ
እንቅስቃሴዎች ሲሆኑ በወሲብ ላይ ጤናማ
የሆነ መልዕክት ያላቸው ናቸው፡፡ ስለዚህ
እነዚህን መልዕክቶች አንብቦ መተርጎምና
በእንቅስቃሴው ውስጥ የራስህን ድርሻ መውሰድ ያንተ ፋንታ ነው፡፡ ሌላው ግን በደንብ
እሷን መከታተልና ነፍስያዋ ማዳመጥ ዋናው
ነገር ነው፡፡ አንድን ሴት አይተህ ከአንተ ምን
እንደምትፈልግ ወሲብ፣ ፍቅር ወይስ ጥልቅ
ቅርርብ የሚለውን ነገር ለማወቅ እነዚህን
ከታች የተዘረዘሩትን ነገሮች ማስተዋልና ነፍሷን ማወቅ ትችላለህ፡፡ ጮክ ብላ
የምትስቅ ከሆነ፣ ከንፈሯን ካረጠበች፣ በጡቷ
ወይም በዳሌዋ ከገፋችህ፣ በጥልቅ
ካዳመጠችህ፣ በኩራት ከተራመደች፣ ዳሌዋን
ካማታች፣ የአይን አሰባበሯ፣ እግሯን አጣምራ
ወደኋላ ከገፋችው፣ ፊቷን ከሸፈነች፣ በጣቶቿ ፀጉሯን ካበጠረች፣ የማይነኩ የሰውነት
ክፍሎችህ ውስጥ እጆቿን ከሰደደች፣
እስቶኪንጓን ካስተካከለች ወይም በሹራቧ
ቁልፍ ስትጫወት፣ በጣም ከዘነጠች
ከተኳኳለችና ሽቶ
ከተጋነነ፣ በጆሮህ በተደጋጋሚ በመምጣት የምታንሾካሹክ ከሆነ ወይም ደግሞ ፍቅራዊ
የሆነ ሌላ መንገድ ከተጠቀመች፣ በጥልቀት
ካፈጠጠችብህ፣ እንዲሁም በአይኗ መዝናህ
ካንተጋር የበለጠ ሰዓት ለማሳለፍ ከፈለገች
በነገሮች ላይ እርግጠና ልትሆንና የራስህን
ውሳኔና እንቅስቃሴ ልታሳልፍ ትችላለህ፡፡

No comments:

Post a Comment