Tuesday, April 30, 2013

ሉሲ ነገ ወደ አገሯ ትመለሳለች


ላለፉት  አምስት ዓመታት በተለያዩ  የአሜሪካ  ግዛቶች በመዘዋወር ኢትዮጵያን ስታስተዋወቅ የቆየችው ሉሲ /ድንቅነሽ/ ነገ ወደ አገሯ ትመለሳለች ።
የባህልና  ቱሪዝም ሚኒስቴር  ለፋና  ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት  እንደገለፀው ፥ ከፍተኛ የመንግስት ባለሰልጣናት  ሉሲ  አገሯ ስትደርስ አቀባበል  ያደርጉላታል ።

የሉሲ ቅርስ ድብቅ የኢትዮጵያ  ሀብት በሚል  ፕሮጀክት ወደ አሜሪካ  ያቀናችው ሉሲ ከሌሎች የኢትዮጵያ  ቅርሶች ጋር በመሆን በተለያዩ  የአሜሪካ  ከተሞች  ለእይታ  ቀርባለች ።

በቆይታዋም ከ350 ሺህ  ሰዎች በላይ ጎብኝተዋታል ተብሎ ።

ሉሲ ለመጨረሻ  ጊዜ በአሜሪካ  ለህዝብ  እይታ የቀረበችው በካሊፎርኒያ  ነው ።

ከሂውስተን የተፈጥሮ ሳይንስ ሙዚየም ጋር በተገባ ስምምነት መሰረት  ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ስታቀናም ፥ ከአገር ከመውጣቷ በፊት ሲቲ  ስካን  እንድትደረግና ምንም  ዓይነት  ጉዳት  እንዳይደርስባት ጥንቃቄ  ተደርጎ  ነው ።
 ምንጭ : ኤፍ ቢ ሲ

No comments:

Post a Comment