Sunday, March 3, 2013

ለታዋቂው አሠልጣኝ ዶክተር ወልደ መስቀል ኮስትሬ ህክምና የሚያስፈልገው 60 ሺህ ዶላር ሊሞላ 295 ሺህ ብር ብቻ ቀረው!

 
ለታዋቂው አሠልጣኝ ዶክተር ወልደ መስቀል ኮስትሬ ህክምና የሚያስፈልገው 60 ሺህ ዶላር ሊሞላ 295 ሺህ ብር ብቻ ቀረው!

የረዥም ርቀት ዋና አሠልጣኝ ሆነው በርካታ ታዋቂና ታላላቅ አትሌቶች በማፍራት የሚታወቁት ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ እግራቸው ላይ የተገጠመው ብረት ምርዘት (ኢንፌክሽን) ፈጥሮባቸው የአልጋ ቁራኛ ከሆኑ ሰነባብቷል፡፡

ለአልጋ ቁራኛ የዳረጋቸው ይኼው የዶክተር ወልደ መስቀል ሕመም፣ በአገር ውስጥ ሕክምና መዳን እንደማይችልና ወደ ውጭ አገር ሔደው ሕክምና እንዲያደርጉ የቅዱስ ያሬድ ሆስፒታል የሕክምና ቦርድ መወሰኑን በተለያዩ ጊዜ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ መገለጹ ይታወሳል፡፡

የሕክምናውን ወጪ በተመለከተ ልጃቸው አቶ ያዕቆብ ወልደ መስቀል እንደገለጸው ከሆነ፣ የሚያስፈልገው 60 ሺሕ ዶላር ነው፡፡ ይህንኑ ለማሟላትም አትሌቶችን ጨምሮ የተለያዩ መንግሥታዋና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የዶክተር ወልደ መስቀልን ሕይወት መታደግ ይችሉ ዘንድ ገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተቋቁሞ እንቅስቃሴ መጀመሩንና ምላሽም እየተገኘ መሆኑን አስረድቷል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ አለባቸው ንጉሤ ፌዴሬሽኑ ለዶክተር ወልደ መስቀል ኮስትሬ ሁትለ መቶ ሺሕ ብር (200,000) የሰጠ ሲሆን ኢትዮጲካሊንክ የተባለው የሬዲዮ ፕሮግራም ትናንት ምሽት ላይ ባደረገው የቀጥታ ስርጭት የገቢ ማሰባሰቢያ መሰናዶ አንድ መቶ አምስት ሺህ ብር (105,000) ማሰባሰብ ችሏል። አሁን የቀረው ሁለት መቶ ዘጠና አምስት ሺህ (295,000) ብር ብቻ ነው። ይህን ታላቅ አሰልጣኝ ለማዳን ሁሉም ወገን ላደረገው ርብርብ ከፍተኛ ምስጋና ሊቸራቸው ይገባል። ቀሪው ገንዘብም በአጭር ጊዜ ውስጥ ተሟልቶ ዶክተሩ ወደ ህክምናቸው የሚሄዱበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ተስፋ አለን።

No comments:

Post a Comment