በቅድመ አክሱም ታሪክ የየሃ ስልጣኔን በ100 ዓመት ወደ ፊት የሚያስቀድምና 2 ሺህ 800 ዓመት ዕድሜ ያለው ጥንታዊ ህንጻ በቁፋሮ ተገኘ።
በየሃ አካባቢ ግራት ቤል ገብሪ በተሰኘ ስፍራ ነው ህንጻው በጀርመናውያንና በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተገኘው።
ግኝቱ በኢትዮጵያና በየመን መካከል ቀድሞ በነበረ ግንኙነት የሚነገሩ መላምቶችን የሚቀይርና የኢትዮጵያን ታሪክ የሚያድስ ይሆናል ነው የተባለው።
ግኝቱ ቀደም ሲል ቋንቋ ላይ የተካሄዱ ምርምሮችንም የሚደግፍ ይሆናል ነው ያሉት።
የሃና አካባቢው ለቱሪዝም መስህብ እንዲሆንና የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲጠበቀም ታስቦ የሚገነባው ሙዚየም የዲዛይን ስራው ተጠናቋል።
በቁፋሮው አብረው የተገኙት የሸክላና የድንጋይ መሳሪያዎችን ጨምሮ ሌሎችም ተንቀሳቃሽ ቅርሶች በዚሁ ሙዚየም የሚቀመጡ ይሆናል።
ጥንታዊውና ታሪካዊው የየሃ ቤተመቅደስ 12 ሜትር ቁመት ሲኖረው በማዕዘን በተጠረቡና 7 ሜትር ርዘመት ባላቸው ድርብ ድንጋዮች ነው ያለምንም ማያያዣ ጭቃና ሲሚንቶ የተገነባው።
ለዘመናት የተፈራረቀበት ፀሃይና ዝናብ በአካባቢው ህይወት ያለው ነገር ካለመኖሩ ጋር ተደማምሮ የጉዳት መጠኑ እየጨመረና አካባቢውም በአረም እየተዋጠ ይገኛል።
የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ኤጀንሲ ስራ አስኪያጅ አቶ ከበደ አማረ እንደሚሉት የጥገናው በፍጥነት መካሄድ ህንጻው ሙሉ በሙሉ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ያስቸለዋል።

No comments:
Post a Comment