Friday, February 8, 2013

6ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የፓትሪያሪክ ምርጫ የካቲት 21 ይካሄዳል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን 6ኛውን የቤተክርስቲያኒቱን ፓትሪያሪክ የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም ትመርጣለች።
የ6ኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የካቲት 18 አምስት እጩ ፓትርያሪኮችን ይፋ እንደሚያደርግም ነው ያስታወቀው።
በምርጫው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያ ሃላፊዎች ፣ የጥንታውያን ገዳማትና አድባራት ተወካዮች ፣ ካህናት ፣ ምዕመናን ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና የማህበረ ቅዱሳን አባላትን የሚወክሉ 800 የሚደርሱ መራጮች ይሳተፋሉ።
የመራጮች ቁጥር ካለፉት አምስት የፓትርያሪክ  መራጮች ጋር ሲነጻጸር የአሁኑ በእጅጉ የላቀ መሆኑንም ነው አስመራጭ ኮሚቴው የተናገረው።
በቀጣይ የካቲት 21 ቀን የሚመረጠው 6ኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ ፓትርያሪክም ምርጫው በተካሄደበት ዕለት ከምሽቱ 12 ሰአት ላይ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል።

No comments:

Post a Comment