Tuesday, February 26, 2013

ፌዴሬሽኑ ለዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ መታከሚያ 200 ሺህ ብር አበረከተ


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለቀድሞው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ እግራቸው ላይ ለደረሰባቸው ጉዳት መታከሚያ የሚውል 200 ሺህ ብር አበረከተ።
ኦሎምፒክን ጨምሮ በተለያዩ አለም አቀፍ ውድድሮች ኢትዮጵያን በአትሌቲክሱ እንድትታወቅ ያደረጉት አንጋፋውና የሃገር ባለውለታ የሆኑት ፥ ዶክተር ወልደመስቀል በ19 90 ዓ.ም ባጋጠማቸው የመኪና አደጋ እግራቸው ላይ ለደረሰባቸው ጉዳት መታከሚያ 1.3 ሚሊየን ብር ያስፈልጋቸዋል።
ከኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና ከአትሌቶች ለህክምና የሚሆን ፥ 720 ሺህ ብር ቢሰበሰብም የታሰበውን ያክል ገንዘብ ሊገኝ አልቻለም።
አሰልጣኙም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በተደጋጋሚ ለህክምና የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግላቸውም ጠይቀዋል።
በዛሬው ዕለትም የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ድጋፉን በተመለከተ ውሳኔ በማስተላለፍ የ200 ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።

No comments:

Post a Comment