Thursday, June 25, 2015

ዕንቁላል፣ ድንችና ቡና ---- share share if

ዕንቁላል፣ ድንችና ቡና
ልጁ ሁልጊዜ እየመጣች ታማርራለች፡፡ ኑሮ አልተሳካልኝም፣ አልሞላልኝም፣ ባሌ ያስቸግረኛል፣ ሥራ ቦታ ሰላም የለኝም፣ ጎረቤቶቼ ረበሹኝ፣ ሕመሙ በረታብኝ፣ ገንዘቤ አልበረክት አለ፤ ጓደኞቼ ያሙኛል፣ ልጆቼ ይበጠብጡኛል፡፡ ስለ ሸረኛ፣ ስለ መጋኛ፣ ስለ ምቀኛ፣ ስለ መተተኛ የማትለው ነገር የላትም፡፡ አባቷ የተለያዩ ታሪኮችን እየጠቀሰ ሊመክራት፣ ሊያጽናናትና ሊያበረታት ሞከረ፡፡ እርሷ ግን ማማረሯን፣ መማረሯንም አላቆመቺም፡፡ እንዲያውም ምሬቷ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ፤ ኑሮዋንም እየጠላቺው፣ ፈተናዋንም እየፈራቺው መጣቺ፡፡
አንድ ቀን መኖር አስጠልቷት፣ ችግሩና መከራም በርትቶባት፣ ምሬቷም ጫፍ ደርሶ መጣቺ፡፡ ‹‹በቃ ከዚህ በኋላ መኖር አልፈልግም፤ ይህንን ያህልስ እኔ ለምን እፈተናለሁ፤ ለምንስ ችግር ይበረታብኛል፤ ለምንስ ሁሉም ነገሮች ይጠሙብኛል፤ በቃ እኔ መኖር የለብኝም›› እያለች ታለቅስ ነበር፡፡
አባቷ ምክሩ ሁሉ እንዳልሠራ፣ የነገራትንም ሁሉ እንደዘነጋቺው ተረዳ፡፡
‹‹ተከተይኝ›› አላትና ወደ ማዕድ ቤት ገቡ፡፡
ወንበር ሰጣትና እርሱ ወደ ምግብ ማብሰያው ሄደ፡፡ ኮመዲኖውን ከፈተና ዕንቁላል፣ ድንችና የተፈጨ ቡና ይዞ መጣ፡፡ እርሷ ግን ትዕግሥቷ አልቆ ነበር፡፡ በልቧም ‹‹እኔ ኑሮ መርሮኝ እርሱ ምግብ ሊጋብዘኝ ይፈልጋል›› ትል ነበር፡፡ ‹‹አባቴ ችግሬን አልተረዳውም ማት ነው፤ ርቦኝ የተነጫነጭኩ መሰለው›› አለቺ፡፡ ‹‹እኔ ምግብ አልፈልግም፣ ቡናም አልጠጣም፤ በቃ እንዲያውም እሄዳለሁ›› አለቺው፡፡ ዝም አላት፡፡
ሦስቱ ምድጃዎች ላይ የሻሂ ማፍያዎችን ጣደ፡፡ በአንደኛው ላይ ዕንቁላሉን፣ በሌላው ላይ ድንቹን፣ በሦስተኛውም ላይ የተፈጨውን ቡና ጨመረው፡፡ ከዚያም ወደ ልጁ መጣና ከጎኗ ተቀመጠ፡፡ ‹‹ምን እየሠራህ ነው፤ የኔ ችግርና ምግብ ምን አገናኛቸው፤ ቤቴ ውስጥ ሞልቷልኮ፤ ሕጻን አደረግከኝ እንዴ፤ ዕድሌ ነው፣ አንተ ምን ታደርግ›› ትነጫነጫለች፣ ትቆጣለች፣ ታማርራለች፡፡ አባቷ ግን ዝም ብሎ ያዳምጣታል፡፡ ማልቀስ ጀመረች፡፡ ትከሻዋን እየደባበሰ ዝም አላት፡፡ ቃል ከአፉ አልወጣም፡፡
ውኃው መንፈቅፈቅ ጀመረ፡፡ አልፎ አልፎም ውኃው ከመክደኛው ወጥቶ እሳቱ ላይ ሲንጠባጠብ ‹ትሽ› የሚለው ድምጽ ይሰማ ነበር፡፡ አባቷ ድንገት ቆመ፡፡ ደንግጣ እንደተቀመጠች አቅንታ አየቺው፡፡ ‹‹በይ ተነሺ› አላት፡፡ ዘገም ብላ ተነሣቺ፡፡
‹‹ሦስቱንም የሻሂ ማፍያዎች ክፈቻቸው›› አላት፡፡
‹‹ለምን?›› አለቺ ግራ ተጋብታ፡፡
‹‹ግዴለም እሺ በይኚ››
መንቀር መንቀር እያለቺ ወደ ማንደጃው ሄደቺ፡፡
‹‹ሦስቱም ማፍያዎች ውስጥ ያሉትን ነገሮች አውጫቸው›› አላት፡፡ ዕንቁላሉንና ድንቹን በጭልፋ አወጣቺና ሰሐኖቻቸው ላይ አደረገቻቸው፡፡ ቡናውን ስኒ ላይ ቀዳቺው፡፡
‹‹እና ምን ይሁን?›› አለቺው ልጁ፡፡
‹‹ድንቹን ተጫኚው፣ ዕንቁላሉን ላጭው፣ ቡናውንም ቅመሺው››
‹‹ተመልከቺ፤ ድንቹ ውኃ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ጠንካራ ነበረ፡፡ የፈላው ውኃ ግን ጠንካራውን ድንች ፈረካከሰው፡፡ ዕንቁላሉ የፈላው ውኃ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ውጩ ጠንካራ ውስጡ ግን ፈሳሽና ስስ ነበረ፡፡ ውኃው ሲፈላ ግን ውስጡ ፈሳሽና ስስ የነበረው አስኳሉ ጠንካራ ሆነ፡፡ ቡናው ሲፈላ ቤቱን በመዓዛው ዐወደው፣ የአካባቢውንም ጠረን ቀየረው፤ ጣዕሙም ልዩ ሆነ፡፡
‹‹ሦስቱም በተመሳሳይ ማፍያ በተመሳሳይ ዓይነት እሳት ነበር የተጣዱት፡፡ ችሀግራቸው አንድ ነው፤ ለአንድ ዓይነት ችግር የሰጡት ምላሽ ግን የተለያየ ነው፡፡ ድንቹ ጥንካሬውን አጣ፣ ዕንቁላሉ አስኳሉ ጠነከረ፣ ቡናው መዓዛውና ጣዕሙን ይበልጥ እንዲያወጣው አደረገው፡፡ ልጄ ያንቺም ችግር ያለው ከገጠመሽ ችግርና ፈተና አይደለም፡፡ ለገጠመሽ ችግርና ፈተና ከምትሰጪው ምላሽ እንጂ፡፡ የተለያዩ ሰዎች አንድ ዓይነት ፈተና ሊገጥማቸው ይችላል፤ እንዲያውም በኑሮው ውስጥ የማይፈተን ሰው የለም፡፡ ነገር ግን ሰዎች ለችግርና ለፈተና የሚሰጡት ምላሽ የተለያየ ነው፡፡
‹‹ፈተና አንዳንዱን እንደ ድንች ጥንካሬውን አጥቶ እንዲፈረካከስ ያደርገዋል፡፡ አንዳንዱን ሰው ደግሞ እንደ ዕንቁላሉ ውስጡን ያጠነክርለታል፤ ሞራሉን ገንብቶ፣ መንፈሱን ያበረታዋል፡፡ እሳት የብረትን ዝገት እንዲያስወግድ ፈተናም የአንዳንዱን የስንፍና ዝገት ያስወግድለታል፣ ውስጡን ጠንካራ ያደርግለታል፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ችግርና መከራው፣ ፈተናና ስቃዩ ውስጣዊ መዓዛውንና ጣዕሙን እንደ ቡናው እንዲያወጣ ያደርገዋል፡፡ ውስጣዊ ችሎታውን፣ ዕምቅ ዐቅሙን፣ የተዳፈነ ተሰጥዖውን፣ ለሌሎች ሊተርፍ የሚችል ጸጋውን ያወጣለታል፡፡
‹‹ውሳኔው በእጅሽ ላይ ነው ልጄ፤ ችግር እንዳይመጣ፣ ፈተናም እንዳይኖር፣ መከራም እንዳይገጥም ተግዳሮትም እንዳይደርስ ማድረግ አይቻልም፡፡ ራስን ወይ ድንች፣ ወይ ቡና ወይም ደግሞ ዕንቁላል ማድረግ ግን ይቻላል፡፡››
ልጁ ጉንጩን ስማው አንገቷን እየነቀነቀች ወጣች፡፡ ውስጧም ‹ዕንቁላል፣ ድንችና ቡና› ይል ነበር፡

Friday, June 19, 2015

ህልም ምንድን ነው? ለምን እናልማለን?

ህልሞች በምንተኛበት ወቅት አዕምሯችን የሚፈጥራቸው የምስሎችና ታሪኮች ውህዶች ናቸው።

ህልሞች የሚያዝናኑ፣ የሚረብሹ፣ ቀልዶች፣ የፍቅር ግንኙነቶች፣ የሚያስፈራሩና አንዳንድ ጊዜም ያልተለመዱ ክስተቶች ሊሆኑ ይችላሉ።

ህልም ለምን እናያለን? ህልም አለማየትስ እንችላለን? ትርጓሜያቸውስ ምንድን ነው? እነዚህና መሰል ጥያቄዎችን አንስቶ የሚተነትነው ሜዲካል ኒውስ ቱደይ በቅርቡ

ህልምን አስመልክቶ የተደረገ ጥናትን ዋቢ አድርጎ ለእነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል።

የህልም እውነታዎች

- ምንም እንኳን የተወሰኑ ሰዎች ያዩትን ህልም በሙሉ የማያስታውሱ ቢሆንም ማንኛውም ሰው በእያንዳንዷ ሌሊት ከ3 እስከ 6 ጊዜ ያህል ህልም ያያል ተብሎ ይታመናል።

- እያንዳንዱ ህልም ከ5 እስከ 20 ደቂቃ ቆይታ እንደሚኖረውም ይነገራል።

- ካየነው ህልም 95 በመቶ የሚሆነው ከመኝታችን ስንነሳ እንረሳዋለን።

- ህልም ማለም የረጅም ጊዜ ትዝታዎቻችን ለማስታወስ ይረዳል።

- ሴቶች ከወንዶች ጋር ሲነጻጻሩ ስለ ቤተሰብ፣ ልጆች እና በቤት ውስጥ ስለሚከናወኑ ነገሮች ነው ህልም የሚያዩት።

- በህልማችን ከምናያቸው ሰዎች መካከል 48 በመቶ የሚሆኑትን መለየት(ማወቅ) እንችላለን።

- አልኮል እንቅልፍንም ሆነ ህልምን የማዘበራረቅ አቅም አለው።

- አይነ ስውራን ህልም ያያሉ፤ ግን በአብዛኛው ከስሜት እና ድምጾች ጋር የተያያዙ ናቸው።

ህልሞች ምንድን ናቸው?

ህልሞች ማንኛውም የሰው ዘር ልጆች በእንቅልፍ ሰአት የምንመለከታቸው ከየእለት ኑሮአችን ጋር የሚገናኝም ሆነ ምንም ግንኙነት የሌላቸው ታሪኮች ወይም ምስሎች እንዲሁም ስሜቶች ቅይጠይ ውጤቶች ናቸው።

ህልሙ የተፈጠረበትና አደረጃጀቱ ማለትም የታሪኩ ፍሰት በአንድ በኩል፤ የህልሞቹ ምንነትና ከአላሚው ጋር ያላቸው ዝምድና ደግሞ በሌላኛው ጠርዝ በሁለት ጎራ የተከፈሉ የህልም አጥኝዎች በህልም ላይ ለሚያደርጉት ጥናት በመነሻነት ያስቀምጡታል።

የኒዩሮ ሳይንስ አጥኝዎች አምስት የእንቅልፍ ደረጃዎችን በማስቀመጥ ህልም የሚከሰተው አይናችን በደንብ በሚርገበገብበት (step 5) ላይ መሆኑን ይናገራሉ።

የእንቅልፍ ምዕራፎች

1. የመጀመሪያው ምዕራፍ - ቀላል እንቅልፍ፣ አይናችን በዝግታ ይንቀሳቀሳል፣ እንዲሁም የአጥንቶቻችን እንቅስቃሴዎች ይቀንሳሉ። ይህ ምዕራፍ ከጠቅላላ እንቅልፋችን ከ4 እስከ 5 በመቶውን ይሸፍናል።

2. 2ኛው ምዕራፍ -  የአይን እንቅስቃሴ ይቆማል፣ የአዕምሮ ሞገዶች እንቅስቃሴ ይዘገያል፣ ከ45 እስከ 55 ከመቶ ይይዛል።

3. 3ኛው ምዕራፍ - በጣም የተዳከሙ የአዕምሮ ሞገዶች (delta waves) ይፈጠራሉ፣ ከ4 እስከ 5 በመቶ የእንቅልፍ ክፍልን ይሸፍናል።

4. 4ኛው ምዕራፍ - በ3ኛው እና 4ኛው ምዕራፍ ተቀስቅሶ የመንቃት እድሉ ዝቅተኛ ነው። ሁለቱም ምዕራፎች የጥልቅ እንቅልፍ (deep sleep) ጊዜያቶች ናቸው። በዚህ ምዕራፍ ምንም አይነት የአይን እና የጡንቻ እንቅስቃሴ አይኖርም።

በዚህ ስአት የሚቀሰቀሱ ሰዎች በፍጥነት የመንቃት እና የመደበት ችግር ያጋጥማቸዋል። ይህም ከአጠቃላይ እንቅልፍ ከ12 እስከ 15 በመቶውን ይሸፍናል።

5. 5ኛው ምዕራፍ - በዚህ ጊዜ የአተነፋፈስና የአይን እርግብግቦሽ ይፈጥናል፤ የቅንድብ ጡንቻዎችም ስራቸውን ያቆማሉ።  የደም ግፊት እና የልብ ትርታም ይጨምራል።

በ5ኛው ምዕራፍ የእንቅልፍ ጊዜ የሚቀሰቀሱ ሰዎች የተለያዩ ያልተለመዱ እና ቅዠት መሰል ታሪኮችን (ህልሞችን) የሚያወሩ ሲሆን፥ ከ20 እስከ 25 በመቶ የእንቅልፍ ጊዜን ይሸፍናል።

የህልሞች ጭብጥ

ወደ መኝታ ክፍላችን ከማምራታችን በፊት የምናስበው ነገር በምናየው ህልም ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል።

ለምሳሌ ተማሪዎች ስለሚወስዷቸው ፈተናዎች፣ በፍቅር ግንኙነት ውስጥ የሚገኙ ሰለ ፍቅረኞቻቸው፣ የግንባታ ባለሙያዎች ደግሞ ስለሚያስገነቧቸው ህንጻዎች ሊያልሙ ይችላሉ።

ህልሞች ከዘወትራዊው ህይወታችን ጋር የመተሳሰር እድላቸው ከፍተኛ ነው።

ህልሞችን ማስታወስ የሚከብደው ለምን ይሆን?

ህልም ካየን ከ5 ደቂቃ በኃላ ከ50 በመቶ የሚሆነውን የምንረሳው ሲሆን፥ ከ10 ደቂቃ በኃላ ደግሞ እስከ 90 በመቶውን እንደምንረሳው ነው የሚታመነው።

የህልም አጥኝዎች እንደሚሉት ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነው ህልም ይረሳል።

ባለሙያዎቹ በነቃንበት ቅጽበት ያየነውን ህልምን ጽፈን ካልያዝነው የመረሳት እድሉ በጣም ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ።

ህልማቸውን የማያስታውሱ እንዳሉ ሁሉ ያዩትን ህልም በምሽት ለመተረክ የማይቸገሩ አንዳንድ ሰዎችም አይጠፉም።

ከረጅም ጊዜ በኃላ ህልም የማስታወስ ልምድ ያላቸውም ሰዎች አሉ።

ሜዲካል ኒውስ ቱደይ ይዞት የወጣውን ሙሉ መረጃ ለመመልከት ከፈለጉ ሊንኩን ይከተሉ http://www.medicalnewstoday.com/
source : FBXC

ህልም ምንድን ነው? ለምን እናልማለን?

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2007(ኤፍ.ቢ.ሲ) ህልሞች በምንተኛበት ወቅት አዕምሯችን የሚፈጥራቸው የምስሎችና ታሪኮች ውህዶች ናቸው።

- See more at: http://www.fanabc.com/index.php/fbc-shows/item/8412-%E1%88%85%E1%88%8D%E1%88%9D-%E1%88%9D%E1%8A%95%E1%8B%B5%E1%8A%95-%E1%8A%90%E1%8B%8D-%E1%88%88%E1%88%9D%E1%8A%95-%E1%8A%A5%E1%8A%93%E1%88%8D%E1%88%9B%E1%88%88%E1%8A%95.html#sthash.WeY5aFyt.dpuf